ሀገሬ
እዚያ ዘመድ አለ
ሁሉም የእናት ልጅ ነው
ሁሉም የአባት ልጅ ነው
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው ያገር ልጅ ሲቸገር
… መቅደስ ነው አገሬ
አድባር ነው አገሬ
እሾህ ነው አገሬ
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ
አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በፀሎት
ለምለም ነው አገሬ
ውበት ነው አገሬ
ገነት ነው አገሬ
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ
ስሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ::
በገብረክርስቶስ ደስታ/ 1953/
No comments:
Post a Comment